የባለአክሲዮኖች የ1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 22 ቀን 2011 ዓ. ም ተካሄደ

የሐሞና ትምህርት ቤት አክሲዮን ማህበር የባለ አክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በህዳር 22 ቀን 2011 ዓ. ም ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ጀምሮ በአፈረነሲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ፣አዲስ አበባ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ።

በጉባዔውም ላይ በቀረቡት ሪፖርቶች የተደረጉት ውይይቶች አክሲዮን ማህበሩ የተቋቋመበትን አላማ እና ርዕይ ስኬታማ እንዲሆን የሚያበረታቱ እና ቦርዱ ጠንክሮ የአጭር እና የረጅም ጊዜ እቅዶቹን እንዲያሳካ የሚረዱ ግብአት እንደሆኑ ተገልጿል፡፡